አስጎብኚዎች ሃይማኖታዊ ቦታዎችን በሚያስጎበኙበት ወቅት ሃማኖታዊ ስነ-ስርዓትን እና አለባበስን መሰረት ያደረገ መሆን እንዳለበት ተገለፀ፡፡ከሰዓት በነበረዉ መድረክ ቱሪዝምና የአስጎብኚነት ስነ-ምግባር ከሃይማኖታዊ ጉብኚት አንፃር በሚል ሁለት ጥናታዊ ፅሁፎች የቀረቡ ሲሆን በክፍል አንድ በአቶ መሀመድ ካሳ እና በክፍል ሁለት በአቶ ፋንታሁን ዋቄ ቀርቧል፡፡ ከሁለቱም ጥናታዊ ፅሁፎች ጥሩ ግንዛቤ እንዳገኙ ተሳታፊዎች ገልፀዋል፡፡
