ኢትዮጵያ በስነ-ፈለክ ምርምር ለአለም ያበረከተችዉን የሳይንስና የፍልስፍና አስተዋጽኦ የቱሪዝም አስጎብኚዎች ሊያስተዋዉቁ ይገባል ተባለ

ቱሪዝም ኢትዮጵያ ባዘጋጀዉ የአስጎብኚዎች ስልጠና ላይ ስነ-ፈለክ ቋንቋና የቀን አቆጣጠር ከቱሪዝም እይታ አንፃር ያለዉ ግንኙነት አስመልክቶ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ ለአስጎብኚዎች ስልጠና የሰጡ ሲሆን በስልጠናዉ ወቅት የስፔስ ቱሪዝም በአለም አቀፍ ተወዳጅ የቱሪዝም አይነት መሆኑን ጠቅሰዉ የስፔስ ቱሪዝም በሀገራችን ቢለመድና ቢስፋፋ ወደፊት አንድ መዳረሻ ሊሆን እንደሚችል ገልፀዋል፡፡ከዚህ በመቀጠልም “Creative Economy’’በሚል ጽንሰ-ሀሳብ ስልጠና የተሰጠ ሲሆን በስልጠናዉም አዳዲስ የቱሪዝም ኢንዱስትሪዎችን በመፍጠር ገቢ እንዴት ማግኘት እንደሚቻል ተገልጿል፡፡ በተጨማሪም ከቱሪዝሙ ዘርፍ አካል ጉዳተኞች ተጠቃሚ መሆን እንዳለባቸዉ ተጠቁሟል፡፡

Leave a Comment