ኢትዮጵያ በቀጣይ የአትሌቲክስ ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ ቱሪዝም ኢትዮጵያ እየሰራ ይገኛል!!

ሀገራችን ያላት ተስማሚ የአየር ሁኔታና መልካም ምድር ከተለያዩ አለማት ለሚመጡ ፕሮፌሽናል ሯጮች ተመራጭ በመሆኗ የቱርክ ብሄራዊ አትሌቲክስ ቡድን ለቶኪዮ ኦሎምፒክ 2020 የሚያደርገዉን ዝግጅት በሱሉልታ ላለፈዉ አንድ ወር ልምምድ ያደረገ ሲሆን ቱሪዝም ኢትዮጵያ ይህን እንደመልካም አጋጣሚ በመጠቀም ሀገራችንን የአትሌቲክስ ቱሪዝም ለማድረግ በሚያደርገዉ ጥረት ከቱርክ ብሄራዊ አትሌቲክስ ቡድን የጋራ ዉይይት፣ የምሳ ግብዣ እና ጉብኝት በእንጦጦ ፓርክ ተካሄዷል፡፡በዚህ ፕሮግራም የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ዳሬክተር አቶ ስለሽ ግርማ እና ማኔጅመንት አባላት የተገኙ ሲሆን በቀጣይነት የቱርክ አትሌቶች ሌሎች ተጨማሪ አትሌቶችን እንዲሁም ቤተሰቦቻቸዉን እና ጓደኞቻቸዉን በመያዝ ሀገራችንን እንደሚጎበኙ እና እንደሚያስተዋዉቁ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡አትሌቶቹ የኢትዮጵያ ህዝብ እንግዳ ተቀባነት፣ ምግብ እና የአየር ፀባይ እንዳስደነቃቸዉ እና እንዳስደሰታቸዉ ገልፀዋል፡፡

Leave a Comment