የኢትዮጵያ ኮንቬንሽን ቢሮ ይፋ ተደረገ!

በቱሪዝም ኢትዮጵያ ስር የተቋቋመው የማይስ ኢትዮጵያ (የኢትዮጵያ ኮንቬሽን ቢሮ )ምስረታ በሀገር አቀፍ ደረጃ ዛሬ በይፋ ተቋቋመ፡፡ ዛሬ በአፍሪካ ኢኮኖሚክስ አዳራሽ በተደረገው የምስረታ ፕሮግራም ላይ ክብርት የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ፤ ክቡር የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትርና የቱሪዝም ኢትዮጵያ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ፣ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትርና የቱሪዝም ኢትዮጵያ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ ኮንቬንሽን ቢሮ በመከፈቱ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክትና ለቢሮው መከፈት እውን መሆን የደከሙትን ሁሉ አመስግነዋል፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሀብት የሚያሳድግ አንድ ዘርፍ እንደሆነ ገልፀው መንግስት ለአጠቃላይ የቱሪዝም ዘርፉ የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረትና በገበታ ለሀገር እንዲሁም በሸገር ፕሮጀክቶች ዘርፉን ለመደገፍ ከፍተኛ አስቷፅኦ እያደረገ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ ክብርት ፕሬዝዳንቷ የማይስ ቱሪዝም ዘርፍም በአግባቡ ከተሰራበት ብዙ ርቀት ልንጓዝበት የምንችልና ውጤታማ ሊያደርገን የሚችል ዘርፍ እንደሆነም አውስተዋል፡፡

Leave a Comment